=<({አል-ኢኽላስ 112:1-4})>=
ﺑﺴﻢ ﺍﻟﻠﻪ ﺍﻟﺮﺣﻤﻦ ﺍﻟﺮﺣﻴﻢ
1. በል! እርሱ አላህ አንድ ነው።
2. አላህ (የሁሉ) መጠጊያ ነው።
3. አልወለደም፤ አልተወለደምም።
4. ለእርሱም አንድም ብጤ የለውም።
![]() =<({አል-ቁርአን 96:1-5})>=
![]() በቡኻሪ በተዘገበው ሐዲስ መሰረት እውቀትን መሻት በእያንዳንዱ ሙስሊም ላይ ግዴታ ነው። ![]() |
---|
በትዕግስት መታነፅ የነዚያ አስከፊ ጊዜያትን በተረጋጋ መንፈስ እና ብርቱ ፍላጎት የሚያስተናግዱ ሰዎች መለያ ነው። እኔና አንተ ካልታገስን ምን ልናደርግ እንችላለን? ከትዕግስት ሌላ መፍትሔ ሊኖረን ይችላልን? ከርሱስ ውጭ ስንቅ ይኖረናልን?
አንድ ታላቅ ሰው ነበር። የችግር ትዕይንቶች የሚፈራረቁበት ፤ መከራዎች የሚሯሯጡበት እና አደጋዎች የሚበዙበት ሆኖም ብዙ ጊዜ ከረመ። እንደምንም ብሎ አንድን መከራ ጊዜ ሲያልፍ ሌላ ይተካበታል። ሆኖም ግን ተስፋ ሳይቆረጥ የትዕግስትን ጋሻ ታጥቆ በአሏህ ላይ ሙሉ ተስፋውን ጥሎ ነበር። እንዲህም ሲል ስለራሱ ይገልፃል:-
ጊዜዬ ከዳኝ ችግሮች እንደሚያልፉና
ክብሬ እንደማይቀንስ ሳያውቅ ቀርቶ
ዘመንም አመፁን ሲያፈራርቅብኝ ከረመ
እኔም በመታገስ አረጋገጥኩ እንደማልሸነፍ ከቶ ብልሆች እንዲህ ነው መከራዎችን የሚያልፋት። አስከፊ ጊዜያትንም ታግለው የሚያሸንፋት።
ከዕለታት አንድ ቀን አቡበከር (ረ.ዐ) ታመው ሳለ የሆኑ ሰዎች ሊጠይቇቸው ገቡ። እንዲህም አሏቸው:- «ሃኪም እንጥራልዎ?» አቡበከርም «ሃኪሙ አይቶኛል» አሉ። «ታዲያ ምን አለ?» አሏቸው። እኔ የፈለግኩትን ሰሪ ነኝ አለ ሲሉ መለሱላቸው።
ከደጋግ ሰዎች ውስጥም አንዱ ታሞ ምንህን ነው ያመመህ ተብሎ ሲጠየቅ እንዲህ አለ:-
ጠያቂዎች ምን እንደሆኑ ሳይረዱ
ነፍሶች በተለለያዩ ህመሞች ይሞታሉ
ወዳጆቻቸውን ትተው የደረሰባቸውን ለሌሎች ስሞታ ያቀረቡም ተሳስተዋሉ
ታገስ መታገስህ በአሏህ ማስቻል እንጂ አይደለምና። የመድህን መምጣትን እርገግጠኛ ስትሆን መጨረሻው የሚያምር መሆኑን አውቀህ ምንዳን የምትከጅል ስትሆን ወንጀሎችህ እንዲማሩልህ እየለመንክ ታገስ። ነገሩ ምንም ቢከፋ ታገስ። መንገዶችም ምንም ቢጨልሙብህ ድል ትዕግስትን ተከትሎ የሚመጣ መሆኑን አውቀህ ድሎት ከችግር በኋላ መሆኑን አውቀህ ከችግር በኋላም ድሎት መኖሩን ተገንዝበህ ታገስ።
በዚህች ዱንያ ውስጥ ያለፋና የትግስታቸው ሃያልነት እና ችግሮችን የመቇቇም ጥንካሬያቸው የሚያስደንቅ ታላላቅ ሰዎችን ታሪክ አንብቤአለሁ። ችግሮች ሲፈራረቁባቸው ከረሙ። እነርሱ ግን የተራሮችን ፅናት ተላብሰው በትዕግስት ያልፏቸው ነበር። ብዙም ሳይቆዩ በትንሽ ጊዜ ውስጥ ፊቶቻቸው ከምቾት ጎህ ፣ ከድል ፣ ከደስታና ከአሸናፊነት ብርሃን ጋር ያበራሉ። ሌላኛው ደግሞ በትዕግስት ብቻ አልተብቃቃም ችግሮችን ተፋለመ ፤ መከራዎችንም ተጋፈጠ ፤ እንዲህ ሲልም ተናገረ:-
ዘመን ሆይ ክብሮች ከሚዋረዱበት መከራዎችህ ያላየኋቸው ካሉህ አምጣቸው እስቲ ልያቸው።
የወጣቱ ተልዕኮ አድራሻ
ኢስላማዊ መጽሐፎችን ያውርዱ |
---|